Adminccsa
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የነጋዳ ሴቶች ማህበር ምክር ቤት "ሴቶች የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ናቸው" በሚል መሪ ቃል የ2017 በጀት ዓመት ጠቅላላ ጉባኤውን በቡታጅራ ከተማ አካሂዷል!
ታህሳስ 16፣ 2018 ዓ/ም ቡታጅራ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የነጋዳ ሴቶች ማህበር ምክር ቤት "ሴቶች የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ናቸው" በሚል መሪ ቃል የ2017 በጀት ዓመት ጠቅላላ ጉባኤውን በቡታጅራ ከተማ አካሂዷል።
የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ባዩሽ ተስፋዬ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ የነጋዴ ሴቶች ማህበር የሴት ነጋዴዎችን ጥቅም በተደራጀ መንገድ የሚያስከብር መሆኑን ገልጸዋል።
ማህበሩ በንግድ ሂደት ውስጥ በሴት ነጋዴዎች ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመቅረፍ በጋራ የሚሰራበት መሆኑንም አመላክተዋል።
ይህንን አደረጃጀት ማጠናከር እና ማጎልበት ወሳኝ መሆኑን የገለጽት ዶ/ር ባዩሽ ማህበሩ ሴቶችን ብሎም የሀገርን ኢኮኖሚ ለማሳደግ የሚኖረዉን አስተዋጾ የበለጠ ለማሳደግ ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ አብራርተዋል።
ለዚህም ቢሮው የሚጠበቅበትን ሁሉ ድጋፍ ያደርጋል ሲሉም ተናግረዋል።
የክልሉ ነጋዴ ሴቶች ማህበር ፕሬዜዳንት ወይዘሮ ምህረት ተስፋዬ ማህበሩ ሴቶች በኢኮኖሚ እድገት ውስጥ የሚጫወቱትን ወሳኝ ሚና በመገንዘብ ለሴቶች ጥቅም የሚሟገትና የንግድ እድሎችን የሚያመቻች ነዉ ብለዋል።
በዚህም ሴቶች በንግዱ ዘርፍ አቅማቸውን እንዲያሳድጉና ለሀገር ሠላም ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ እገዛ አድርጓል ብለዋል።
የሴቶች የኢኮኖሚ አቅም እንዲጠናከርና ተወደዳሪ እንዲሆኑ፣ የቁጠባ ባህላቸውን እንዲያድግና በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ከሚገኙ አቻ ማህበራት ጋር ጤናማ ግንኙነት እንዲፈጠሩና ምርታቸውን እንዲያስተዋውቁ ምክንያት ሆኗል ሲሉ ወይዘሮ ምህረት ተናግረዋል ።
ማህበሩ ከክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ጋር በመቀናጀት በህገ ወጥ ስራ ቁጥጥር የበኩሉን ሚና እየተጫወተ ይገኛል ብለዋል።
በጉባኤው የተከናወኑት ተግባራት ዝርዝር ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን በውይይት መድረኩም ችግሮቹ ተለይተው የመፍትሄ አቅጣጫ እንዲቀመጡ ተደርጓል።
በመጨረሻም የክልሉ የነጋዴ ሴቶች ማህበር እንዲቋቋም አስተዋጾ ላበረከቱ አካላት የእዉቅናና የምስጋና መርሃ-ግብር በማካሄድ ጉባኤዉ ተጠናቋል።
መረጃው የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ነው
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት (Central Ethiopia Chamber of Commerce )
ስልክ ቁጥር :- 0919391139፣ 0943048874
ኢ-ሜል :- cethiopia@gmail.com